አዲስ አበባ | መስከረም 15 2016| NBC ETHIOPIA – ህብረተሰቡ የበዓል ወቅትን ተጠቅመው በሀሰተኛ የብር ኖት ግብይት ከሚፈጽሙ ወንጀለኞች ሊጠነቀቅ እንደሚገባ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አሳስቧል፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በመግለጫው፤ በበዓላት ወቅት የሚፈጸሙ ግብይቶች ጥድፊያና ግርግር የሚበዛባቸው በመሆኑ ወንጀለኞች ለማጭበርበር ስራቸው እንደ መልካም አጋጣሚ እንደሚጠቀሙበት አመላክቷል፡፡
ከዚህ አኳያ በቀጣይ ቀናት የሚከበሩ ኃይማኖታዊና ህዝባዊ በዓላትን ምክንያት በማድረግ በሚፈጸሙ ግብይቶች ላይ ወንጀለኞች በስፋት ሊሳተፉ እንደሚችሉም ጠቁሟል፡፡
እንደ ኢፕድ ዘገባ የገንዘብ ኖቶች ላይ ያሉ የደህንነት ምልክቶችን በጥንቃቄ በመመልከት ግብይት መፈጸም እንደሚገባም ባንኩ አስታውቋል፡፡
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook-https://www.facebook.com/ethiopiannbc/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv
#NBC_ETHIOPIA
#ሆኖ_መገኘት










