አዲስ አበባ | መስከረም 14 2016| NBC ETHIOPIA -የ31 አመቱ ጣልያናዊ በ194ኛው የሰሜን ለንደን ደርቢ አርሰናል ከ ቶተንሃም ሁለት እኩል በተለያዩበት ጨዋታ አርሰናል ላይ ለተቆጠረችው ሁለተኛዋ ድርሻ እንደነበረው አይዘነጋም።

ጆርጊኒሆ በኢንስታግራም ገጹ ላይ ባሰፈረው መልእክት፣ በእርሱ ስህተት ክለቡን ሁለት ውድ ነጥቦችን ማሳጣቱን ገልጿል።
“ከባድና ዋጋ የሚያስከፍል ስህተት ሰርቼ ሳለ ጓደኞቼ፣ አሰልጣኜ፣ የክለቡ ሰራተኞችና ደጋፊዎች በሃፍረት ካቀረቀርኩበት ቀና እንድል ያደረጉበት መንገድ ከፊቴ ለሚጠብቀኝ ጠንካራ ስራ መነሳሳት ይሆነኛል፣ ምርጡና ጠንካራው ጆርጊኒሆ ይገባችኋልና” ብሏል።
የክለቡ ዋና አሰልጣኝ ሚካኤል አርቴታ በበኩላቸው ከጨዋታው በኋላ በሰጡት ቃለ መጠይቅ፣ “መሳሳት የእግር ኳሱ አካል በመሆኑ ከጆርጊኒሆ ጎን ነን እንወደዋለን” ብለዋል።
መሳሳት በተመልካች አይን ሲታይ ቀላል ቢመስልም ለተጨዋቾች ግን እየተጫወቱ እስከሆነ ድረስ ይፈቀድላቸዋል ባይ ናቸው አሰልጣኙ።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv











