Tuesday, November 17, 2026
  • Login
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
No Result
View All Result
Home News

ልጆች የላም ወተት መቼ መጀመር አለባቸው?

September 25, 2023
in News
0 0
0
Share on FacebookShare on TwitterShare on Telegram

፡፡ ፡፡ ፡፡ ፡፡

አዲስ አበባ | መስከረም  14 2016| NBC ETHIOPIA -በስራ ገበታ ላይ እያሉ ቀላል የማይባሉ እናቶች አዉቀውም ሆነ ሳያውቁ “የጡቴ ወተት በቂ ስላልሆነ ለልጄ የላም ወተት ተጨማሪ ጀምሬለታለው” ብለው ሳያበቁ ልጁ ተውከት ና ተቅማጥ ታመው ማየት የተለመደ ነገር ነው ።

ልጆች የላም ወተት መቼ ነዉ መጀመር ያለባቸው? ጤናማ የሆነ የልጅ አመጋገብ ምንድነው?

ህፃናት የተስተካከለ አካላዊና አዕምሮዊ እድገት እንዲኖራቸዉ ጤናማ የአመጋገብ ዘዴ ጉልህ ድርሻ አለዉ፡፡ ይህ ጤናማ የሆነ የአመጋገብ ዘዴ  ልጆቹን ከተለያዩ በሽታዎች እንደ ተቅማጥ ፣ የሳምባ ምች ፣ የጀሮ ምርቀዛ (‘ኢንፌክሽን’) እና ሌሎችንም ተላላፊ በሽታዎች በመከላከል ከፍተኛ የሆነ አስተዋፅኦ አለዉ፡፡

ጤናማ  የአመጋገብ ዘዴ የምንላቸዉ ምንድናቸው?

– የመጀመሪያዎቹ 6 ወራት ዕድሜ

በዚህ የዕድሜ ክልል ዉስጥ ህፃናት ያለምንም ተጨማሪ ምግብ የእናት ጡት ብቻ በቀን ከ8-12 ጊዜ እንዲወስዱ ይመከራል፡፡ጨቅላ ህፃናት ወዲያዉ በተወለዱ በ30 ደቂቃ ዉስጥ የእናት ጡት መጀመር አለባቸዉ፡፡

በተለምዶ በተለይ በገጠራማዉ አካባቢ እንዲሁም በከተማዎች አልፎ አለፎ ጨቅላ ህፃናት ወዲያዉ እንደተወለዱ  ከእናት ጡት በፊት የሚሰጡ (prelactal feeding) እንደ አብሽ ፣ ቅቤ ፣ ሻይ ፣ ዉሃ በስኳር የመሳሰሉትን መስጠት ለኢንፌክሽን ስለሚያጋልጣቸዉ ጎጂ ባህላዊ ልማድ ነዉ፡፡

– ከስድስት እስከ አስራ ሁለት ወራት ዕድሜ

በዚህ የዕድሜ ክልል ዉስጥ ህፃናት ከእናት ጡት በተጨማሪ ሌላ ምግብ መጀመር አለባቸዉ፡፡

እድሜያቸዉ ከ 6-8 ወር ለሆኑ ህፃናት ተጨማሪ ምግቦችን በፈሳሽ መልክ (እንደ አጥሚት) በቀን ከ2-3 ጊዜ እንዲሁም ከ8-12 ወር ለሆናቸዉ በከፊል ጠጣር መልክ (እንደ ገንፎ) በቀን 4-5 ጊዜ መመገብ ያስፈልጋል፡፡

በዚህ የዕድሜ ክልል ዉስጥ ጡት ማጥባት የሚቀጥል ሲሆን ነገር ግን የእናት ጡት ወተት መጠን እየቀነሰ የሚሄድበት ጊዜ ስለሆነ ለህፃናት የሚሰጠዉ ተጨማሪ ምግብ በዓይነትም በመጠንም በደንብ መጨመር አለበት፡፡ ተጨማሪ ምግቦችን በጠጣር መልክ (እንደ እንጀራ፣ ዳቦ፤ እንቁላል፣ ሥጋ፣ ወዘተ የቤተሰብ ምግቦችን) መጀመር  ይቻላል፡፡

– ከስድስት ወር ቀደመው ሌላ ነገር ቢጀምሩ ምን የጤና ችግር ይገጥማቸዋል?

????ልጆች ብዙ ወይም በቂ የእናት ጡት እንዳያገኙ ያደርጋቸዋል::

????ልጆች ለተቅማጥ በሽታ ያጋልጣቸዋል:: 

– ተጨማሪ ምግብ ከስድስት ወር አልፈው ቢጀምሩ እሳ?

???? ልጆች የሚያስፈልጋቸውን ተጨማሪ ሀይልና ንጥረ ምግቦች እንዳያገኙ ያደርጋል፡፡

???? ልጆች ለመቀጨጭና  ለተለያዩ የማእድን እጥረት ሊጋለጡ ይችላሉ፡፡

ልጆች የላም ወተት መቼ ነዉ መጀመር ያለባቸው?

– ህጻናትን ቶሎ የላም ወተት ማስጀመር ያለው የጤና ጉዳት

የአለም ጤና ዲርጅትና የተለያዩ ጥናቶች እንደሚያሳዩት   የተለየ አስገዳጅ ሁኔታ ካልተፈጠረ በስተቀር የላም ወተት ከአንድ አመት በፊት መሰጠት የለበትም፡፡ ከአንድ አመት በፊት የላም ወተት የሚወስዱ ህፃናት በተለይም መጠኑ ከ20 ounce ወይም ግማሽ ሊትር በላይ ከሆነ የአንጀት መድማትና አይረን የተባለዉን ንጥረ ነገር ከአንጀት ወደ ደም እንዳይመጠጥ በማድረግ በአይረን እጥረት ምክንያት የሚከሰት የደም ማነስ (Iron deficiency anemia) ያመጣል፡፡

– የላም ወተት ለልጆች በቶሎ ማስጀመር የጤና ጉዳቶች

o ዝቅተኛ የአይረን መጠን ስላለው ለደም ማነስ ችግር ያጋልጣል

o ከፍተኛ የፕሮቲን ይዘት ስላለው ለአንደኛው የስኳር ህመም ያጋልጣቸዋል

o የህጻናት ሆድ ድርቀት

o የወተት አለርጂ

o ላክቶዝ ንጥረነገር በሰውነት ውስጥ አለመኖር በወተት ውስጥ ለሚገኘው የላክቶዝ ንጥረነገር መብላላት አለመቻል ያጋልጣቸዋል፡፡

o ተቅማጥ የመሳሰሉትን የጤና እክሎች ያመጡባቸዋል

በሃና ተሰማ

YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA

TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia

Website – https://nbcethiopia.com/news/

Facebook- https://www.facebook.com/ethiopiannbc

#NBC_ETHIOPIA

#ሆኖ_መገኘት

ShareTweetShare
Previous Post

የጉራጌ ባህላዊ እሴቶችን በዩኔስኮ ለማስመዝገብ እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ

Next Post

ጣሊያናዊው የአርሰናል አማካይ ጆርጊኒሆ ለክለቡ ቤተሰቦችና ደጋፊዎች ምስጋናውን አቅርቧል

Related Posts

የትኩረት ማጣትና መቅበጥበጥ ተግዳሮቶች ፡ በዶክተር ዮሐንስ ባህረ ጥበብ
Hard Talk

የትኩረት ማጣትና መቅበጥበጥ ተግዳሮቶች ፡ በዶክተር ዮሐንስ ባህረ ጥበብ

November 17, 2026
25
COP32 የኢትዮጵያን የአየር ንብረት አጀንዳ ለማራመድና ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ትልቅ ዕድል ይፈጥራል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
News

COP32 የኢትዮጵያን የአየር ንብረት አጀንዳ ለማራመድና ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ትልቅ ዕድል ይፈጥራል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

November 16, 2026
9
መርካቶ የበጎነት መንደር፦ ማህበራዊ ፍትህ በተግባር፣ የዜጎች ሕይወት በእውነት ሲቀየር!
News

መርካቶ የበጎነት መንደር፦ ማህበራዊ ፍትህ በተግባር፣ የዜጎች ሕይወት በእውነት ሲቀየር!

November 16, 2026
8
በ2026/27 የባርሴሎና እና የሪያል ማድሪድ ተቃራኒ ነጥቦች
News

በ2026/27 የባርሴሎና እና የሪያል ማድሪድ ተቃራኒ ነጥቦች

November 16, 2026
16
ህወሃት የሚመራው ጥምረት የፈረሰው የተቋቋመ ዕለት ነው! – የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ
Hard Talk

ህወሃት የሚመራው ጥምረት የፈረሰው የተቋቋመ ዕለት ነው! – የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ

November 13, 2026
52
ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ባይተዋር አይደለችም! – የመካከለኛው ምስራቅና ኤዢያ ፓስፊክ ጉዳዮች ከፍተኛ ተመራማሪ አንተነህ ጌታቸው (ዶ/ር)
News

ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ባይተዋር አይደለችም! – የመካከለኛው ምስራቅና ኤዢያ ፓስፊክ ጉዳዮች ከፍተኛ ተመራማሪ አንተነህ ጌታቸው (ዶ/ር)

November 13, 2026
38
Next Post
ጣሊያናዊው የአርሰናል አማካይ ጆርጊኒሆ ለክለቡ ቤተሰቦችና ደጋፊዎች ምስጋናውን አቅርቧል

ጣሊያናዊው የአርሰናል አማካይ ጆርጊኒሆ ለክለቡ ቤተሰቦችና ደጋፊዎች ምስጋናውን አቅርቧል

ከአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ መምሪያ ዕዝ የተሰጠ ወቅታዊ መረጃ ቁጥር 5

ፍቅር ሰላም አንድነት የክብረ በዓላት በረከት

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026
የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

November 17, 2026

Popular Posts

  • የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • አልማዝ ባለጭራ (Herpes zoster)

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • ሱስ ምን ማለት ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • በአለም ላይ ያሉ አስገራሚ ሁነቶች

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ማለፊያ ውጤት ይፋ ተደረገ

    0 shares
    Share 0 Tweet 0

Follow Us:

Facebook Youtube
National Media

Follow Us:

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026

Company

  • About Us
  • Career
  • Advertising

Contact Us

Mesqel Square Road, Addis Ababa, Ethiopia.
+251 970707143
+251 970707142
Email: info@nbcethiopia.com

  • Apps
  • Terms & Policy

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

No Result
View All Result
  • Home
  • NEWS
    • NEWS SHOW
    • NEWS
    • NEWS PROGRAM
  • PROGRAM AND FEATURE
    • Holiday
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • LIVE
  • English
    • English
    • Amharic

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

Welcome Back!

Login to your account below

Forgotten Password?

Create New Account!

Fill the forms bellow to register

All fields are required. Log In

Retrieve your password

Please enter your username or email address to reset your password.

Log In

Add New Playlist

Are you sure want to unlock this post?
Unlock left : 0
Are you sure want to cancel subscription?