አዲስ አበባ | መስከረም 8 2016| NBC ETHIOPIA- የዩክሬን ጦርነት መቼ እንደሚያበቃ መወሰን የሚችሉት የሩሲያ እና የዩክሬን ፕሬዚዳንቶች ብቻ ናቸው ሲሉ የቱርኩ ፕሬዝዳንት ኤርዶጋን ያስታወቁ ሲሆን አክለውም፤ ፑቲን ይህንን ጦርነት በተቻለ ፍጥነት ለማቆም ከወሰኑ ከጎናቸው እንደሚሆኑ ተናግረዋል፡፡

ይህ ጦርነት መቼ እንደሚቆም ወይም ለምን ያህል ጊዜ እንደሚቆይ የቀን መቁጠሪያ መስጠት አስቸጋሪ እንደሚሆንና ጉዳዩ የሁለቱም መሪዎች ይሁንታ ብቻ የሚወስነው መሆኑን ነው የገለጹት፡፡
ስለ ጦርነቱ ሁኔታ አስተያታቸውን የተጠየቁት ፕሬዝዳንት ኤርዶጋን ግጭቱ ለረዥም ጊዜ ሊቀጥል እንደሚችልም የተናገሩት ፡፡
ጦርነቱ በተቻለ ፍጥነት እንዲያበቃ እኛ በጣም ተስፋ ማድረግ እንፈልጋለን ፤ ስለዚህ ፑቲን በተቻለ ፍጥነት ይህንን ጦርነት እንዲያቆሙ ጠይቀዋል። ፕሬዚዳንቱ በመጨረሻም ሩሲያ እንደ ምዕራባውያን እምነት የሚጣልባት ሀገር እንደሆነች አስታውቀዋል።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram –https://t.me/nbcethiopiatv