በአዲስ አበባ | መስከረም 7 2016| NBC ETHIOPIA- ከተማ ደረጃ በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ስር የሚገኙ የግልና የመንግስት ትምህርት ተቋማት ከፍተኛ የከተማና የክፍለ ከተማ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት የ2016 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ይፋዊ የማስጀመሪያ መርሀ ግብር ተካሄደ።

በመርሀ ግብሩም ከትምህርት ማስጀመር በተጓዳኝ የተማሪዎች ምገባም የተጀመረ ሲሆን በተያዘው አመት ተማሪዎች በስነ-ምግባር የታነፁና ለነገዋ ሀገር ሁለንተናዊ እድገት ለውጥ አሻራቸውን እንዲያኖሩ እንዲሁም ከመቼውም ጊዜ ይልቅ የመማር ማስተማሩን ሂደት በማሳለጥ ተማሪዎች ውጤታማ እንዲሆኑ የሚያስችል አቅም መፍጠርላይ በትኩረት እንደሚሰራ ተገልጿል።
ቢሮው በማህበራዊ ትስስር ገጹ ባሰፈረው መልዕክት ትምህርት መጀመሩን አስታውቆ ለሁሉም የትምህርት ማህበረሰብ ለትምህርት ዘመኑ እንኳን አደረሳችሁ ብሏል።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram –https://t.me/nbcethiopiatv












