አዲስ አበባ | መስከረም 5 2016| NBC ETHIOPIA-ኢትዮጵያ በአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን አህጉራዊና አካባቢያዊ የመሠረተ ልማት ትስስሮች ልዩ ቴክኒካል ኮሚቴን በሊቀመንበርነት እንድትመራ ተመረጠች።


የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን እ.ኤ.አ ከሴፕቴምበር 12-15 2023 በዛንዚባር ታንዛኒያ ሲካሄድ በቆየው 4ኛው የልዩ ቴክኒካል ኮሚቴ ስብሰባ ላይ ኢትዮጵያ 4ኛውን የልዩ ቴክኒካል ኮሚቴን ለሚቀጥሉት ሁለት ዓመታት በሊቀመንበርነት እንድትመራ በሙሉ ድምጽ ተመርጣለች፡፡
በዚህ 4ኛው የልዩ ቴክኒካል ኮሚቴ ስብሰባ ወቅት በህብረቱ ኮሚሽን አማካኝነት የሚከናወነው የአፍሪካ የመሠረተ ልማት ፕሮግራም /Program for infrastructure Dvelopment/ ለቀጣዮቹ 10 ዓመታት እንዲራዘም ከመደረጉ በተጨማሪ ሁሉንም ዓይነት የትራንስፖርት ዘዴ/መንገድ፤ አየር፤ባቡርና ማሪታይም /የሚመለከቱ በርካታ መርሀግብሮች መጽደቅ መቻላቸውን የትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ በርኦ ሀሰን አሳውቀዋል፡፡
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook- https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram -https://t.me/nbcethiopiatv
#NBC_ETHIOPIA
#ሆኖ_መገኘት












