የአዲስ አበባ | መስከረም 4 2016| NBC ETHIOPIA- ዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ በሚቀጥለው ሳምንት ዋይት ሀውስን ይጎበኛሉ ተብሎ እንደሚጠበቅና ከአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ጋር እንደሚገናኙ ዘገባዎች አመልክተዋል።

ነገርግን ትክክለኛ የጊዜ ገደብ እና ተጨማሪ ዝርዝሮች አልገለጹም።
ዜለንስኪ በኒውዮርክ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ እና የጥቁር ባህር እህል ስምምነትን ለማደስ በሚደረገው ጥረት ላይ ለመወያየት ከተባበሩት መንግስታት ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ጋር የሁለትዮሽ ስብሰባዎችን እንደሚያደርጉ መረጃዎች እየወጡ ነው።
ዘለንስኪ በዋሽንግተን ዲሲ በሚያደርጉት ቆይታ ካፒቶል ሂልን ይጎበኛል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን፤ ባይደን ኮንግረሱ ለዩክሬን 24 ቢሊዮን ተጫማሪ ዶላር ለወታደራዊ እና ሰብአዊ እርዳታ እንዲያፀድቅ ይጠይቃሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ አናዶሉ ዘግቧል።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc/
Telegram –https://t.me/nbcethiopiatv