አዲስ አበባ | መስከረም 2 2015| NBC ETHIOPIA- የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን እና የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን በሩሲያ ምስራቃዊ ክፍል ተገናኝተው እየመከሩ መሆኑ ታውቋል።

ፑቲን በሩሲያ አሙር ክልል ቮስቶችኒ ከተማ በሚገኘው ዘመናዊ የሮኬት ማስወንጨፊያ ማዕከል ኪምን ሲቀበሏቸው ስላገኘውህ ደስ ብሎኛል ብለዋል።
መሪዎቹ በአስተርጓሚዎች ሰላምታ ሲለዋወጡ የተደመጠ ሲሆን፤ የሮኬት ማስወንጨፊያ ቦታውንም ጎብኝተዋል።
የሩሲያው ፕሬዚዳንት ሩሲያ ሰሜን ኮሪያን ሳተላይት እንድትገነባ ትረዳ እንደሆነ በጋዜጠኞች ሲጠየቁ፤ ፑቲንም ሲመልሱ ወደዚህ የመጣንበት ዋናው ምክንያት ለዚህ ነው፤ ኪም ለሮኬት ኢንጂነሪንግ ከፍተኛ ፍላጎት አለው፡፡ ሀገራቸው ጠፈር ለማልማት በመሞከር ላይ ናት ሲሉ መለስዋል።
ኪም በበኩላቸው ሁልጊዜ የፕሬዚዳንት ፑቲንን ውሳኔ እንደግፋለን እንዲሁም ኢምፔሪያሊዝምን በመዋጋት ላይ አብረን እንሆናለን ብለዋል ።
ቢቢሲ እንደዘገበው ሩሲያ በዩክሬን ላይ የምታደርገውን ወረራ ለማገዝ ሁለቱ መሪዎች የጦር መሳሪያ ስምምነት ሊያደርጉ ይችላሉ ተብሎ ተሰግቷል።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc/
Telegram – https://t.me/nbcethiopiatv