አዲስ አበባ | መስከረም 2 2015| NBC ETHIOPIA- ኢትዮጵያውያን በእያንዳንዱ የሕይወታቸው ምዕራፍና በ365 እያንዳንዱ ቀናት ሽክርክሪት ለሀገር፣ ለወገንና ለዓለም የሚጠቅም ታሪክ ሊጽፉ እንደሚገባ የጥንታዊ መዛግብት ተመራማሪ እና ጸሃፊ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ ገለጹ።

ዶ/ር ሮዳስ አዲሱን ዓመት አስመልክተው እንደገለጹት፤ ዘመን ኡደት፣ ሽክርክሪት ጉዞ ነው። በዘመን አንቆምም እንሄዳለን። ሁሉም ተንቀሳቃሽ ነው። ጸሃይ፣ ጨረቃም ይንቀሳቀሳል። በስራና በሕይወት ለውጥ እንቅስቃሴ ማድረግ ያስፈልጋል።
አዲስ ዓመት አዲስ ማንነት ይዘን የምንጓዝበት ነው ያሉት ዶ/ር ሮዳስ፤ ከኡደት ጋር አብረን መሄድ አለብን። አምላክ በየዓመቱ 365 ገጽ ያለበት ምንም ያልተጻፈበት ንጹህ ወረቀት ሰጥቶናል ማለታቸውን ኢፕድ ዘግቧል።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook- https://www.facebook.com/ethiopiannbc/
Telegram – https://t.me/nbcethiopiatv











