አዲስ አበባ | ጳጉሜ 6 2015| NBC ETHIOPIA -የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ለመላው የሀገራችን ህዝቦች፣ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች አመራሮች፣ አባላትና ደጋፍዎች ከሁሉም በማስቀደም እንኳን ከ2015 ዓ.ም ወደ 2016 ዓ.ም አሸጋገራችሁ ይላል::

በአዲሱ ዓመት በፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል፣ በመንግስትና በፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል አብሮ የመስራት የፖለቲካ ባህል የሚዳብርበት እና ለፖለቲካ ፓርቲዎች እንቅስቃሴ አስቻይ ሁኔታ የሚፈጥር የፖለቲካ ምህዳር እንዲኖር የጋራ ምክር ቤቱ የተቻለውን ሁሉ ያደርጋል::
2016 ዓ.ም በሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች ሠላምና መረጋጋት የሚፈጠርበት የሠላም፣ የደስታና ተድላ ዓመት እንዲሆንልን የጋራ ምክር ቤቱ ይመኛል።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc/
Telegram – https://t.me/nbcethiopiatv