አዲስ አበባ | ጳጉሜ 4 2015| NBC ETHIOPIA- ጳጉሜን 4 ከሸማችነት ወደ አምራችነት በሚል መሪ ስያሜ በአዲስ አበባ ከተማ የአምራችነት ቀን እየተከበረ ይገኛል።

ቀኑን ምክንያት በማድረግ የኤግዚቢሽንና ባዛር በኢትዮ ኩባ ወዳጅነት አደባባይ ተከፍቷል።
በመክፈቻው መርሃግብር ላይ ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ እና የስራ፣ ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጃንጥራር አባይ የዘላቂ ልማታችንና ህልውናችን ቁልፍ የሆነዉ አምራችነት በመሆኑ ከሸማችነት ወደ አምራችነት በመሸጋገር የሀገርን ኢኮኖሚ መገንባት ይገባል ብለዋል።
የከተማ አስተዳደሩ የተለያዩ የንግድ ማዕከላትን በመገንባት ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ለማድረግ እየሰራ እንደሆነ የገለፁት አቶ ጃንጥራር በቀጣይ የኢንዱስትሪዎችን ምርታማነት ለማሳደግ መንግስት የሚጠበቅበትን ድጋፍ እንደሚያደርግ ገልፀዋል።
የአዲስ አበባ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ቡዜና አልከድር በበኩላቸው አምራች ኢንዱስትሪዎችን ለማጠናከር በሃገር ምርት በመኩራትና የገበያ ትስስር ማጠናከር ይገባል ያሉ ሲሆን አምራቾች ከጠባቂነት ተላቀው ተወዳዳሪ አምራች መሆን እንዳለባቸውም ገልፀዋል።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram – https://t.me/nbcethiopiatv












