አዲስ አበባ | ጳጉሜ 3 2015| NBC ETHIOPIA-በሰሜን ምስራቅ ማሊ ጽንፈኛ እስላማዊ ታጣቂዎች በሕዝብ ማመላለሻ ጀልባ ላይ በፈጸሙት ጥቃት 49 ሰላማዊ ሰዎችን መግደላቸውን የሀገሪቱ ግዚያዊ መንግሥት አስታወቀ።
ጽንፈኛ ቡድኑ በወታደራዊ ጦር ሰፈር ላይም ጥቃት ፈጽሞ 15 ወታደሮችን መግደሉን ገልጿል።

ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሰዎች በዚህ ጥቃት መገደላቸው ይገለጽ እንጂ በሰሜን ማሊ በምትገኘው ቲምቡክቱ ከተማ ባለፉት ሳምንታት በሕዝብ መጓጓዣ የትራንስፖርት አማራጮች ላይ ተደጋጋሚ ጥቃቶች ሲፈጸሙ ቆይተዋል።
እንደ ማሊ መንግሥት ከሆነ ታጣቂዎቹ ኒጀር ተብሎ በሚጠራው ወንዝ ከጋኦ ወደ ሞፕቲ ከተማ እየተጓዘ በነበረ የሕዝብ ማመላለሻ ጀልባ ላይ ጥቃት ከፍተው ነው 49 ሰላማዊ ሰዎቹን የገለዱት።በጀልባ የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጠው ኩባንያ ለፈረንሳይ የዜና ወኪል ሲናገር የጀልባው የሞተር ክፍል ቢያንስ በሦስት ሮኬቶች ዒላማ ተደርጓል ብሏል።

ከዚያም ታጣቂዎቹ መንቀሳቀስ ወዳቃተው ጀልባ በመግባት ተሳፋሪዎችን ማስወረዳቸውን ቢቢሲ፤ የኤኤፍፒ የዜና ወኪል ምጮችን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል።
ወታደራዊ ቡድኑ የቀድሞውን ፕሬዝዳንት ኢብራሂም ኬይታን ከስልጣን አውርዶ መንበሩን ከያዘ በኋላ ሰፊ ድጋፍ አግኝቶ ነበር።
ወታደራዊ ቡድኑ አገሪቱን ማስተዳደር ከጀመረ ወዲህ አነስተኛ በሚባል ደረጃ በአገሪቱ የጽንፈኛ እስላማዊ ታጣቂዎች እንቅስቃሴን መግታት ችሏል።ከእአአ 2012 ጀምሮ ከአል-ቃዒዳ እና ከእስላሚክ ስቴት ጋር ግንኙነት ያላቸው ጽንፈኛ እስላማዊ ቡድኑ በሰሜናዊ ማሊ ይንቀሳቀሳሉ።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Website – https://nbcethiopia.com/news/
Telegram – https://t.me/nbcethiopiatv
#NBC_ETHIOPIA
#ሆኖ_መገኘት