አዲስ አበባ | ጳጉሜ 1 2015| NBC ETHIOPIA-ዛሬ እየተከበረ ያለውን የአገልጋይነት ቀን በማስመልከት የጤና ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማት በአዲስ አበባ በመስቀል አደባባይ ነጻ የጤና ምርመራ እየሰጡ ይገኛሉ።

አገልግሎቱን የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ በመስቀል አደባባይ ያስጀመሩ ሲሆን፣ በፕሮጋራሙ ላይ ሚኒስትሮችን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች ተሳትፈዋል።

የነጻ የጤና ምርመራው የልብ፣ ቀዶ ጥገና፣ ከአንገት በላይ፣ የአይን፣ የጥርስ፣ የጡትና የማህጽን በር፣ የስኳር፣ የአልትራሳውንድ፣ የአእምሮ፣ የውስጥ ደዌና ሌሎች ምርመራዎችን የሚያካትት ሲሆን፣ በመላ ሀገሪቱ በአንድ ቀን 200ሺህ ሰዎችን ለማገልገል እንደታሰበም ኢ ፕ ድ በዘገባው አስታውቋል።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc/
#ሆኖ_መገኘት












