አዲስ አበባ | ጳጉሜ 1 2015| NBC ETHIOPIA-ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ፤ ሀገራቸውን ከ38 ዓመታት በላይ ላገለገሉ የፌዴራል ተቋማት ሰራተኞች እውቅና እና ሽልማት አበርክተዋል።

በመርሃ ግብሩ ላይ ከ38 ዓመታት በላይ ሀገራቸውን ያገለገሉት አምባሳደር ግርማ ብሩ፣ አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ እና አቶ ተክለወልድ አጥናፉ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ልዩ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚሁ ሁነት ላይ ባስተላለፉት መልእክትም ከቤተሰብ ጀምሮ ሀገርን ማገልገል መታደል መሆኑን በመግለጽ በአገልግሎታቸው ላበረከቱት አስተዋጽኦ አመስግነዋል። አክለውም ሀገርን በታማኝነት ማገልገል የህይወት ዘመን ትልቁ ስጦታ መሆኑን ጠቅላይ ገልፀዋል።
በዚህ ልክ ሀገርንና ህዝብን ማገልገል ልዩ ስጦታ መሆኑን ጠቅሰው እናንተ ሀገርን በታማኝነት በማገልገላችሁ ለትውልዱ አሻራችሁን አሳርፋችኋልና ልተኮሩ ይገባችኋል ብለዋል።

በዛሬው እለት በአዲስ አበባ የሚገኙ የታክሲ አሽከርካሪዎች ለተወሰኑ ሰዓታት ህዝብን በነጻ በማገልገል ያሳዩት አገልጋይነት የእናንተን ፈለግ መከተላቸውን መሳያ ነው ሲሉ ተናግረዋል።
የማገልገል ውጤት የህይወት ዘመን ኢንቨስትመንት በመሆኑ አደራችሁን በብቃት በመፈፀም የሀገር ባለውለታ ስለሆናችሁ ኢትዮጵያ ምንጊዜም ታመሰግናችኋለች ብለዋል።
ኢትዮጵያ አሁን ላይ በፈተና ውስጥ ብትሆንም ዘላቂ ሰላሟና ብልጽግናዋ ተረጋግጦ የተሻለ ነገ እውን መሆኑ አይቀርም ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@admin
Facebook -facebook.com/ethiopiannbc/










