አዲስ አበባ |ነሐሴ 29 2015| NBC ETHIOPIA- በስካይ ስፖርትስ ተንታኝነት እየሰራ የሚገኘው ኪን ትላንት ምሽት አርሰናል በሜዳው ማንችስተር ዩናይትድን ሶስት ለአንድ የረታበት ጨዋታ ከተጠናቀቀ በኋላ ወደ ሜዳ ለመግባት ሲሞክር ነው ድብደባው የተፈጸመበት።

አንድ የአርሰናል ደጋፊ መተላለፊያው ውስጥ ሮይ ኪንን በጭንቅላቱ( በቴስታ) ሲመታው የሚያሳይ ተንቀሳቃሽ ምስል በማህበራዊ ሚዲያ እየተዘዋወረ ነው።
ዴይሊ ሜይል እንደዘገበው ኪን በሞያ ባልደረባው ሚካህ ሪቻርድስና የጸጥታ አካላት ርብርብ ከተጨማሪ ጥቃት ተርፏል።የ52 ዓመቱ አየር ላንዳዊ ከአውሮፓውያኑ 1993-2005 ድረስ ለኦልትራፎርዱ ክለብ መጫወቱ ይታወሳል።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc/












