አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 26/2015፣ NBC ETHIOPIA-በመንግስትና የግል አጋርነት ትብብር በየአብ ሜዲካል ሴንተር ኤንደ ሪሀብልቴሽን ሊሚትድ ፤ አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮና የዳግማዊ ምኒሊክ ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ጋር በሦስትዮዉሽ ስምምነት የሚሰራ የኩላሊት እጥበት ማዕከል በግበዓት እጥረት የተነሳ ላለፉት ሶስት ሳምንታት አገልግሎት ማቋረጡ ይታወሳል።

በከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ ድጋፍ ፤ የአብ ሜዲካል ሴንተር ኤንደ ሪሀብልቴሽን ሊሚትድ ፤ ጤና ቢሮና ሆስፒታሉ እንዲሁም በሌሎች አጋር ድርጅት ያላለሰለሰ ጥረት በዛሬዉ እለት አገልግሎት መስጠት መጀመሩን ተገልጿል ሲል አዲስ ሚድያ ኔትወርክ በዘገባው ገልጿል።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc/











