አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 25/2015፣ NBC ETHIOPIA -በመግለጫው በመጠናቀቅ ላይ ባለው 2015 ዓ.ም እንደሀገር የተሰሩ ስኬታማ ስራዎችና ተግዳሮቶች የተነሱ ሲሆን ስንዴን ወደውጭ መላክ የተጀመረበት፣ የሰሜኑን ጦርነት ለማስቆም የሰላም ድርድር የተከናወነበት እንዲሁም በአለም አቀፍ በዲፕሎማሲያዊ ስኬት ያስመዘገበችነትና የብሪክስ ህብረትን የተቀላቀለችበት ከስኬታማ ተግባራት መካከል መሆናቸው ተገልጿል ።

በአንዳንድ የሀገሪቱ ክፍሎች የሰላም መደፍረስ፣የኑሮ ውድነትና የመልካም አስተዳደር እጦት በበጀት አመቱ የታዩ ተግዳሮቶች እንደነበሩም ተነስቷል ።
የ2016 አዲስ አመት የአከባበር ሁኔታ በተመለከተ ማብራሪያ የተሰጠ ሲሆን በዚህም መሰረት የጳጉሜ ቀናትን ስያሜ በመስጠት በመላው ሀገሪቱ ቀናቶቹ በተሰጣቸው ስያሜ መሰረት እንደሚከበሩ ተገልጿል ።
በዚህም መመሰረት
???? ጳጉሜ አንድ የአገልግሎት ቀን
???? ጳጉሜ ሁለት። የመስዋዕትነት ቀን
???? ጳጉሜ ሶስት የበጎነት ቀን
???? ጳጉሜ አራት የአምራችነት ቀን
???? ጳጉሜ አምስት የትውልድ ቀን
???? ጳጉሜ ስድስት የአብሮነት ቀን ተብሎ እንደሚከበሩ ተገልጿል ።
በሰላማዊት ወልደገሪማ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc/












