አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 25/2015፣ NBC ETHIOPIA- ከንቲባ አዳነች አቤቤ በደቡብ ኮሪያ ቹንቾን ከተማ ከሚገኘው ታዋቂው ኮያንግፖኦክ ዩኒቨርስቲ(KNU) ፕሬዘደንት ኪም ሂዎን ያንግ ጋር ተወያይተዋል::

በውይይታቸውም በሁለቱ እህት ከተሞች መካከል በተደረሰው ስምምነት መሰረት የከንቲባ ነፃ የትምህርት እድል ፕሮግራም (Mayor’s Scholarship Program) ማመቻቸት በሚቻልባቸው መንገዶች ዙሪያ የተወያዩ ሲሆን የKNU ዩኒቨርስቲ መስፈርት ለሚያሟሉና የተሻለ ውጤት ለሚያስመዘግቡ የአዲስ አበባ ተማሪዎች በከንቲባ የተሰየመ ነፃ የትምህርት እድል ለመስጠት ተስማምቷል::
የከንቲባ ነፃ የትምህርት እድል (Mayor’s Scholarship program) የከተማ አስተዳደሩ የአዲስ አበባ እህት ከተሞች ውስጥ ከሚገኙ ታዋቂ ዩኒቨርሲቲዎች ጋር በመተባበር በከተማችን ለሚገኙ በትምህርታቸው የተሻለ ውጤት ለሚያስመዘግቡ ተማሪዎች የነፃ የትምህርት እድል ለመስጠት በከንቲባ አዳነች አቤቤ የተጀመረ እንቅስቃሴ ሲሆን ለከተማችን ተማሪዎች መልካም እድል የሚፈጥር ይሆናል።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ የደቡብ ኮርያ ቹንቾን ከተማ የስራ ጉብኝታቸውን አጠናቅቀው ወደ አዲስ አበባ ተመልሰዋል::
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc/












