አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 25/2015፣ NBC ETHIOPIA- ነጩ ቤተመንግስት ፒዮንግያንግ ከሞስኮ ጋር ያላትን የጦር መሳሪያ ድርድር ማቆም አለባት ሲል አስታውቋል። የአሜሪካ የብሄራዊ ደህንነት ቃል አቀባይ ጆን ኪርቢ እንደተናገሩት ዩናይትድ ስቴትስ በሩሲያ እና በሰሜን ኮሪያ መካከል ሊደረጉ ስለሚችሉ የጦር መሳሪያ ስምምነቶች አሳስቧታል ብለዋል።

ኪርቢ አክለውም የሩስያ መከላከያ ሚኒስትር ሰርጌይ ሾጉ ሰሜን ኮሪያን በጎበኙበት ወቅ ከ ኪም ጆንግ ኡን ጋር በተገናኙበት ወቅት ፒዮንግያንግ የመድፍ ጥይቶችን ለሞስኮ እንድትሸጥ ለማሳመን መምከራቸውን ገልፀዋል።
እንደ አልጀዚራ ዘገባ ነገር ግን የአሜሪካ ቃል አቀባይ መረጃውን እንዴት እንደሰበሰቡት ዝርዝር ከመስጠት ተቆጥበዋል።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook –https://nbcethiopia.com/news/