አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 25/2015፣ NBC ETHIOPIA- ማንችስተር ሲቲ ፖርቱጋላዊውን የዎለቨርሃምፕተን አማካይ ማቲየስ ኑኔዝ በ55 ሚሊዮን ዩሮ የዝውውር ሂሳብ ለማስፈረም ተስማምቷል።

ሲቲ ከ55 ሚሊዮን ዩሮ በተጨማሪ ቶሚ ዶይሊን በረጅም የውሰት ዉል ለዎልቭስ ለመስጠት ተስማምቷል።
ዎልቭስ ዶይሊን በ5 ሚሊዮን ዩሮ የዝውውር ሂሳብ በቋሚነት የማስፈረም አማራጭ ቀርቦለታል።
ዶይሊ በ2022-23 የውድድር አመት በውሰት ለሸፊልድ ተጫውቶ አሳልፏል።
ማቲየስ ኑኔዝ በአምናው የክረምት የዝውውር መስኮት ነበር ከፖርቱጋሉ ስፖርቲንግ ሊዝበን በ42 ሚልዮን ፓውንድ ወደ እንግሊዙ ክለብ የተዘዋወረው።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook-https://www.facebook.com/ethiopiannbc/












