በአዲስ አበባ፣ ነሐሴ 23/2015፣ NBC ETHIOPIA ኮሪያዋ ቹንቾን ከተማ ቆይታቸወ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለጀግኖች ኢትዮጵያውያን የኮሪያ ዘማቾች በቆመላቸው የመታሰቢያ ሃውልት ስር የአበባ ጉንጉን በማስቀመጥ ጀግኖቻችንን ዘክረዋል ።

ከንቲባዋ ባስተላለፉት መልዕክት፤ ከራሳቸው አልፈው ለዓለም ሰላም ፣ ለሰው ልጆች ነጻነትና ክብር በጀግንነት በወደቁ አባቶቻችን ታሪክ ኢትዮጵያዊያን በዓለም አደባባይ እንድንኮራ አድርጎናል ሲሉ በማህበራዊ ሚዲያ ገጻቸው ገልጸዋል::
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc












