በአዲስ አበባ፣ ነሐሴ 23/2015፣ NBC ETHIOPIA “ስለ አዲስ አበባ ቱሪዝም እንምከር” በሚል መሪ ቃል በአዲስ አበባ ባህል ኪነጥበብና ቱሪዝም ቢሮ የተዘጋጀ የዉይይት መድረክ እየተካሄደ ነዉ።

ዉይይቱ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር እየተደረገ ሲሆን በመድረኩ ለዉይይቱ ግብዐት ብሎም ለቀጣይ ስራዎች የሚያግዙ ሰነዶች ቀርበዋል።
አዲስ አበባ ከአፍሪካ ህብረት መዳረሻነት ባለፍ የተለያዩ ለቱሪዝም ምንጭ የሚሆኑ መዳረሻዎች በዉስጧ አሉ። ያላትን የቱሪዝም ሀብት ወደ ኢኮኖሚ ለመቀየርና ከተማዋን እንዲሁም ኢትዮጵያን ተጠቃሚ ለማድረግ በርካታ ስራዎች ይጠበቃሉ ተብሏል።

በየአመቱ ወደ 22 ሚሊዮን የሚጠጉ መንገደኞች አዲስ አበባን እረግጠዉ ያልፋሉ ይህም ለከተማዋ ትልቅ ከቱሪዝም የሚገኝ የገቢ ምንጭ መሆን ይችላል ነዉ የተባለዉ። በመድረኩ የሀገር ዉስጥ ቱሪዝም ያሉትን ባህሪያት እና ጥቅም እንዲሁም የአዲስ አበባን የቱሪዝም ሀብት ለማሳደግ የተወሰዱ እርምጃዎችና መፍትሄዎች ተገልፀዋል።
ከዘርፉ የሚገኘዉን ጥቅም ለማሳደግ መንግስት፣ ባለድርሻ አካላትና ማህበረሰቡ ሀላፊነት ወስደዉ መሳተፍ እንዳለባቸዉ ተነስቷል።
ሊያ ክብሮም
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc












