በአዲስ አበባ፣ ነሐሴ 22/2015፣ NBC ETHIOPIA – በ19ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ ለተሳተፈው ልዑካን ቡድን ነገ አቀባበል እንደሚደረግ የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር አስታወቀ።

የባህልና ስፖርት ሚኒስትሩ አቶ ቀጄላ መርዳሳ በሰጡት መግለጫ እንዳሉት በሃንጋሪ ቡዳፔስት በተካሄደው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፕዮና ኢትዮጵያ ጥሩ ውጤት ያገኘችበት ነው ።
በተገኘው ውጤት ለመላው ኢትዮጵያዊያን እንኳን ደስ አላችሁ ያሉት ሚኒስትሩ ለአትሌቲክስ ልዑኩ ነገ 23/2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 12 ጀምሮ ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ አቀባበል ይደረጋል ብለዋል።
በቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ከጠዋቱ 12 ሰዓት እስከ 2 ሰዓት የሚደረገውን አቀባበል ቀጥሎ አትሌቶቹ በአውራ ጎዳናዎች በመዘዋወር ከህዝቡ ጋር ደስታቸውን እንደሚገልጹ ኢዜአ ዘግቧል።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc/
#NBC_ETHIOPIA
#ሆኖ_መገኘት