በአዲስ አበባ፣ ነሐሴ 22/2015፣ NBC ETHIOPIAየኒጀር ወታደራዊ አስተዳደር በዋና ከተማዋ ኒያሚ የሚገኘውን የፈረንሳይ ኤምባሲ ምንም ዓይነት የምግብ ፤ ውሃ እና ኤሌክትሪክ አቅርቦት አቋርጧል መባሉን በርካታ ማህበራዊ ሚዲያዎች እየዘገቡት እንደሚገኝ ታውቋል፡፡

የብሔራዊ ድጋፍ ኮሚቴ ለብሔራዊ ጥበቃ ምክር ቤት (CNSP) ፕሬዝዳንት ኤልህ ኢሳ ሃሱሚ ቡሬማ በኒጀር የሚገኙ የፈረንሳይ የጦር ሰፈር አጋሮች ምንም ዓይነት አገልግሎት እንዳያገኙ ትዕዛዝ አስተላልፈዋል፡፡
በተጨማሪም ማንኛውም አካል ፈረንሳውያንን የሚያግዝ ከሆነ “የሉዓላዊነት ጠላት” እንደሆነ በሪፖርቱ ተካቷል፡፡
ሪፖርቶቹ የወጡት በወታደራዊ አስተዳደሩ ለፈረንሳዩ አምባሳደር ሀገሪቱን ለቀው እንዲወጡ የሁለት ቀን ቀነ ገደብ ካለቀ በኋላ ነው እንደሆነ የዘገበው አናዶሉ የዜና ወኪል ነው ።
በሃና ተሰማ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc