አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 18/2015፣ NBC ETHIOPIA – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት ኢትዮጵያ የብሪክስ አባል ሀገር መሆኗ መልካም አጋጣሚ ነው ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያ ሁሉን አካታችና ብልጽግና የሰፈነበት ዓለም አቀፋዊ ስርዓትን ለመፍጠር በሚደረገው ጥረት የራሷን አስተዋጽኦ ለማበርከት ዝግጁ ናት ሲሉም አረጋግጠዋል በመልዕክታቸው ።
በደቡብ አፍሪካ እየተካሄደ ያለው 15ኛው የብሪክስ አባል ሀገራት ጉባኤ ኢትዮጵያን ጨምሮ፥ አርጀንቲና፣ ግብጽ፣ ኢራን፣ ሳዑዲ አረቢያን እና የተባበሩት አረብ ኢሚሬቶችን በአዲስ አባልነት ተቀብሏል።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc












