አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 17/2015 ፣ NBC ETHIOPIA – ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከትምህርት ሚኒስትር ፕ/ር ብርሀኑ ነጋ ጋር በከተማዋ የትምህርት ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል።

በውይይታቸውም የትምህርት አሰጣጡን በማዘመን እና በእውቀትና በስነ ምግባር የታነጸ ትውልድ ለማፍራት የከተማ አስተዳደሩ እየሰራቸው ያሉ ስራዎች አበረታች መሆናቸውን ፕ/ር ብርሃኑ ጠቅሰዋል::

ከውይይታቸው በኃላ እድሳትና መልሶ ግንባታ ብቻ ሳይሆን ዘመኑን የዋጀ እንዲሁም ወቅቱ የደረሰበትን ዘመናዊ ቴክኖሎጂ በመጠቀም የተደራጀ የመብራት ፣ የአየር መቆጣጠሪያ ፣ ዘመናዊ የውስጥ መገልገያ ዕቃዎች ፣ የመሰብሰቢያ አዳራሾች እና ለተገልጋይ ቅርብና ክፍት የሆኑ ምቹ የመስሪያ ቦዎች የተካተቱበት ከተማዋን እንዲመጥን ተደርጎ የታደሰውን የከንቲባ ጽ/ቤት ተዘዋውረው ጎብኝተዋል፡፡
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc