አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 17/2015 ፣ NBC ETHIOPIA – ህንድ የጨረቃ ተልእኮዋን በጨረቃ ደቡብ ዋልታ ክልል ላይ በማሳረፍ የመጀመሪያዋ ሀገር በመሆን ታሪክ ሰርታለች።

በዚህም ህንድ ከአሜሪካ፣ከቀድሞዋ ሶቪየት ዩኒየን እና ከቻይና ቀጥሎ ጨረቃ ላይ በማረፍ ከሀገራቱ ጎራ ትቀላቀላለች።
ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ “ሌላ ሀገር የማይችለው ቦታ ላይ ደርሰናል” ብለዋል። ሚስተር ሞዲ በBRICS ጉባኤ ላይ ከሚሳተፉበት ደቡብ አፍሪካ ሆነው ዝግጅቱን በቀጥታ ሲከታተሉ እንደ ነበር ታውቋል።የሮቦቲክ ላንደር በተሳካ ሁኔታ ንክኪ ካደረገ በኋላ በመላው ህንድ ክብረ በዓል ተካሂዷዋል።
በሃና ተሰማ
ምንጭ(ቢቢሲ)
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc/











