አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 16/2015 ፣ NBC ETHIOPIA – የአፍሪካ ህብረት ባለፈው ወር በኒጀር የተካሄደውን ወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት ተከትሎ ኒጀርን ከማንኛውም የህብረቱ እንቅስቃሴ አግዷል።

ይህ ውሳኔ ይፋ የሆነው የአፍሪካ ህብረት የሰላም እና የፀጥታ ምክር ቤት በኢትዮጵያ ዋና ከተማ አዲስ አበባ ውስጥ ከተካሄደ በኋላ፣ በሀምሌ 26 ፕሬዝዳንት መሀመድ ባዙምን ከስልጣን በወረዱበት መፈንቅለ መንግስት ምክንያት በርካታ ምዕራባውያን ሀገራት ለኒጀር የሚሰጡትን እርዳታ ካቋረጡ በኋላ ነው።
የአፍሪካ ህብረት የሰላም እና የፀጥታ ምክር ቤት ሁሉም አባል ሀገራቱ እና አለም አቀፉ ማህበረሰብ በኒጀር ስልጣን በሀይል የተቆጣጠረውን ጁንታ ህጋዊ ሊያደርግ ከሚችል ከማንኛውም እርምጃ እንዲቆጠቡ አሳስቧል።
ህብረቱ የመፈንቅለ መንግስቱ መሪዎች ተመራጩን ፕሬዝዳንት ሞሃመድ ባዙምን እንዲፈቱ በድጋሚ ጥሪ አቅርቧል።
የምዕራብ አፍሪካ ሀገራት የኢኮኖሚ ማህበረሰብ (ኢኮዋስ) ከዚህ ቀደም ወታደራዊ እርምጃ እንደሚወስድ መግለጹ ይታወሳል።
በሃና ተሰማ
ምንጭ(አልጀዚራ)
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc












