አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 15/2015 ፣ NBC ETHIOPIA -የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የስነ-ምግባር እና የጸረ ሙስና ኮሚሽን የሚታመን እና የሚተማመን ትውልድ ለመፍጠር በሚል መሪ ሀሳብ ከኪነጥበብ ባለሙያዎች ጋር የፖናል ውይይት እያካሄደ ይገኛል።

በውይይቱም በትዉልዱ ዙሪያ እየመነመነ የመጣውን የስነምግባር ችግርን ለመቅረፍ: ለአገሪቷ እድገት ነቀርሳ የሆነውን ሙስና ለማጥፋት እና ማህበረሰቡን ለማንቃት ቤተሰብ: የሀይማኖት ተቋማት: የትምህርት ተቋማት: የኪነጥበብ ባለሙያዎች ትልቅ አስተዋጾ ስላላቸው በጋራ ሊሰሩ ይገባል ብሏል ኮሚሽኑ።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc/