Tuesday, November 17, 2026
  • Login
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
No Result
View All Result
Home News

ሂዩማን ራይትስ ዎች የሳኡዲ ድንበር ጠባቂዎችን  በጅምላ ግድያ  ከሰሰ

August 21, 2023
in News
0 0
0
Share on FacebookShare on TwitterShare on Telegram

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 15/2015 ፣ NBC ETHIOPIA -የሳዑዲ ድንበር ጠባቂዎች በመቶዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያንን መግደላቸውን ሪፖርቱ  ጠቁሟል።

በጦርነት እየታመሰች ካለችው የመን ወደ ሳዑዲ አረቢያ ድንበር ለማቋረጥ የሞከሩ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ኢትዮጵያውያንን የሳዑዲ ድንበር ጠባቂዎች መግደላቸውን የሂማን ራይትስ ዋች ሪፖርት አመልክቷል።

ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት ሂዩማን ራይትስ ዋች ከመጋቢት 2014 ዓ.ም. እስከ ሐምሌ 2015 ዓ.ም. ድረስ ቢያንስ በመቶዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በሳዑዲ የድንበር ጠባቂዎች መገደላቸውን አስታውቋል።

ስደተኞችን መግደል የሳዑዲ መንግሥት ፖሊስ አካል ከሆነ ግድያዎቹ በሰብዓዊነት ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎች ናቸው ብሏል ሂዩማን ራይትስ ዋች።

በአንዳንድ አጋጣሚዎች የሳዑዲ ድንበር ጠባቂዎች ስደተኞችን የትኛውን የሰውነት ክፍላችሁን እንምታ ብለው ጠይቀው  በጥይት እንደሚመቷቸው በሪፖርቱ ተካቱዋል።

የድንበር ጠባቂዎቹን ጥቃት በመሸሽ ወደ የመን ድንበር በሚሸሹ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ላይም ተቀጣጣይ ነገር እንደሚተኩሱባቸው የመብት ድርጅቱ አመልክቷል።

ሂዩማን ራይትስ ዋች ከመጋቢት 2014 እስከ ሐምሌ 2015 ድረስ ከየመን ወደ ሳዑዲ ለመሻገር የሞከሩ 38 ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን ካነጋገረ እና ከ350 ያላነሱ ተንቀሳቃሽ ምስሎች እንዲሁም ፎቶግራፎችን በተጨማሪም የሳተላይት ምስሎችን ከተመለከተ በኋላ ነው ይህን ሪፖርት ያወጣው።

በአሁኑ ወቅት ድህነት እና ግጭትን በመሸሽ ከ750ሺህ ያላነሱ ኢትዮጵያውያን በሳዑዲ አረቢያ እንደሚኖሩ የሂዩማን ራይትስ ዋች መረጃ ያሳያል።

የመብት ተሟጋች ቡድኑ ከእ.ኤ.አ 2014 ጀምሮ ድንበር ላይ የሚፈጸሙ ግድያዎችን የመረመረ ሲሆን፣ ግድያዎች የጨመሩበት ሁኔታ ግድያዎቹ ሆነ ተብለው እንደሚፈጸሙ ያሳያል ብሏል።

ስደተኞች እንደሚሉት የኤደን ባሕረ ሰላጤን በአነስተኛ ጀልባዎች ከተሻገሩ በኋላ የየመን ሰው አዘዋዋሪዎች በሁቲ አማጺያን ቁጥጥር ሥር ወደምትገኘው እና ለሳዑዲ ድንበር ቅርብ ወደሆነችው ሳዳ ግዛት እንደሚያሻግሯቸው ይናገራሉ።

በርካታ ስደተኞች ከሳዑዲ ጋር እየተዋጉ የሚገኙት የሁቲ አማጺያን እና ሕገ-ወጥ ሰው አዘዋዋሪዎቹ በጥምረት እንደሚሠሩ ገልጸው፤ በትውልድ የመናውያን የሆኑት አዘዋዋሪዎች ለሁቲ አማጺያን ካስረከቧቸው በኋላ አማጺያኑ ወደ ማጎሪያ ካምፖች ካስገቧቸው በኋላ “የመውጫ” ገንዘብ እንደሚከፍሉ ስደተኞቹ ይገልጻሉ።

ስደተኞች እንደሚሉት አብዛኛውን ጊዜ በቁጥር 200 የሆኑ ሰዎች በአንድ ላይ በመሆን ድንበር ለማቋረጥ ሙከራ የሚያደርጉ ሲሆን፣ ወላጆቻቸው አብረዋቸው የሌሉ ሕጻናት እና ሴቶች ያሉባቸው ቡድኖች ድንበር ለመሻገር ሲሞክሩ ጥቃት ይደርስባቸዋል።

ስደተኞቹ የሳዑዲን ድንበር እንደተሻገሩ ሞርታር እና ሌሎች ፈንጅዎች በሳዑዲ ወታደሮች እንደሚተኮሱባቸው ይገልጻሉ።

በሳዑዲ ድንበር ጠባቂዎች በቁጥጥር ሥር የሚውሉም በእስር ቤቶች ለወራት ታስረው እንደሚቆዩ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ጨምረው ተናግረዋል።

ሂዩማን ራይትስ ዋች ፀረ ፈንጅ የሆኑ እና ከባድ መሳሪያ የተገጠመባቸው ወታደራዊ ተሸከርካሪዎች የታጠቀ የሳዑዲ ድንበር ጥበቃ ድንበር ላይ ጥበቃ ሲያደርግ ባገኘው የሳተላይት ምስል ማረጋገጡን ገልጿል።

የጥቃቱ ሰለባ የሆኑት ስደተኞች “አካላቸው ስለሚቆራረጥ ማንነታቸውን መለየት እንኳን አዳጋች የሆኑ በርካቶች አሉ” ብሏል አንድ ለመብት ተሟጋች ቡድኑ ቃሉን የሰጠ ስደተኛ።

ሂዩማን ራይትስ ዋች ሕይወታቸው ያለፈ እና በጽኑ የተጎዱ ስደተኞች ምሥሎች እና ቁጥራቸው እየጨመረ የመጣ የመቃብር ስፍራዎችን የሚያሳዩ ቪዲዮችን ማመሳከር ችሏል።

ኢንተርናሽናል ሪሃብሊቴሽን ካውንስ ፎር ቶርቸር ቪክትምስ የተባለ ተቋም መርማሪዎች በምሥሎች ላይ የሚታዩ ሰዎች የተጎዱት ወይም ሕይወታቸው ያለፈው በፍንዳታ፣ በጥይት በመመታት እና በቃጠሎ መሆኑን አረጋግጠዋል።

ሂዩማን ራይትስ ዋች ያነጋገራቸው ስደተኞች ድንበር ጠባቂዎቹ ከቅርብ ርቀት  ተቀጣጣይ መሳሪያ እንደተኮሱባቸው እና በብረት እንደሚደበድቧቸው ተናግረዋል።

አንድ የ17 ዓመት ስደተኛ የሳዑዲ ድንበር ጠባቂዎች እርሱ እና ሌላ ስደተኛ ሁለት ሴት ስደተኞችን እንዲደፍሩ እንዳስገደዷቸው ተናግሯል። ይህ ታዳጊ ስደተኛ አንዲት ስደተኛን አልደፍርም ያለን ሌላ ስደተኛ መግደላቸውን ጨምሮ ተናግሯል።

ሂዩማን ራይትስ ዋች ሳዑዲ አረቢያ ስደተኞችን እና ጥገኝነት ጠያቂዎችን መግደል በአስቸኳይ ማቆም አለባት ብሏል።

የሚመለከታቸው ተቋማት እና መንግሥታትም ሳዑዲ ይህን ፖሊሲዋን እንድታቆም እና ተጠያቂነት እንዲሰፍን ጫና መፍጠር አላቸው ሲል አሳስቧል።

ሂዩማን ራይትስ ዋች ጉዳዩ ያሳስበናል የሚሉ መንግሥታት በሳዑዲ እና በሁቲ አመራሮች ላይ ማዕቀቦችን መጣል ይኖርባቸዋል ያለ ሲሆን፣ በስደተኞች ላይ የተፈጸመው ግድያ በሰብዓዊነት ላይ ከሚፈጸም ወንጀል ጋር የሚመደብ በመሆኑ  በተባበሩት መንግሥታት የሚደገፍ አጣሪ ቡድን መቋቋም አለበት ብሏል።

በሃና ተሰማ

YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA

TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia

Facebook-https://www.facebook.com/ethiopiannbc/

#NBC_ETHIOPIA

#ሆኖ_መገኘት

ShareTweetShare
Previous Post

አዲስ ቱሞሮ ፕሮጀክት

Next Post

የ10 ዓመት የልማት ዕቅድ መካከለኛ ጊዜ አፈጻጸም ግምገማ ተጀመረ

Related Posts

የትኩረት ማጣትና መቅበጥበጥ ተግዳሮቶች ፡ በዶክተር ዮሐንስ ባህረ ጥበብ
Hard Talk

የትኩረት ማጣትና መቅበጥበጥ ተግዳሮቶች ፡ በዶክተር ዮሐንስ ባህረ ጥበብ

November 17, 2026
25
COP32 የኢትዮጵያን የአየር ንብረት አጀንዳ ለማራመድና ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ትልቅ ዕድል ይፈጥራል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
News

COP32 የኢትዮጵያን የአየር ንብረት አጀንዳ ለማራመድና ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ትልቅ ዕድል ይፈጥራል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

November 16, 2026
9
መርካቶ የበጎነት መንደር፦ ማህበራዊ ፍትህ በተግባር፣ የዜጎች ሕይወት በእውነት ሲቀየር!
News

መርካቶ የበጎነት መንደር፦ ማህበራዊ ፍትህ በተግባር፣ የዜጎች ሕይወት በእውነት ሲቀየር!

November 16, 2026
8
በ2026/27 የባርሴሎና እና የሪያል ማድሪድ ተቃራኒ ነጥቦች
News

በ2026/27 የባርሴሎና እና የሪያል ማድሪድ ተቃራኒ ነጥቦች

November 16, 2026
16
ህወሃት የሚመራው ጥምረት የፈረሰው የተቋቋመ ዕለት ነው! – የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ
Hard Talk

ህወሃት የሚመራው ጥምረት የፈረሰው የተቋቋመ ዕለት ነው! – የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ

November 13, 2026
52
ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ባይተዋር አይደለችም! – የመካከለኛው ምስራቅና ኤዢያ ፓስፊክ ጉዳዮች ከፍተኛ ተመራማሪ አንተነህ ጌታቸው (ዶ/ር)
News

ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ባይተዋር አይደለችም! – የመካከለኛው ምስራቅና ኤዢያ ፓስፊክ ጉዳዮች ከፍተኛ ተመራማሪ አንተነህ ጌታቸው (ዶ/ር)

November 13, 2026
38
Next Post

የ10 ዓመት የልማት ዕቅድ መካከለኛ ጊዜ አፈጻጸም ግምገማ ተጀመረ

የጆን ስቶንስ ጉዳት

የጆን ስቶንስ ጉዳት

የሀገር መከላከያ ሠራዊት በጅግጅጋ ከተማ የሁለት ሚሊዮን ብር ድጋፍ አበረከተ

የሀገር መከላከያ ሠራዊት በጅግጅጋ ከተማ የሁለት ሚሊዮን ብር ድጋፍ አበረከተ

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026
የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

November 17, 2026

Popular Posts

  • የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • አልማዝ ባለጭራ (Herpes zoster)

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • ሱስ ምን ማለት ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • በአለም ላይ ያሉ አስገራሚ ሁነቶች

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ማለፊያ ውጤት ይፋ ተደረገ

    0 shares
    Share 0 Tweet 0

Follow Us:

Facebook Youtube
National Media

Follow Us:

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026

Company

  • About Us
  • Career
  • Advertising

Contact Us

Mesqel Square Road, Addis Ababa, Ethiopia.
+251 970707143
+251 970707142
Email: info@nbcethiopia.com

  • Apps
  • Terms & Policy

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

No Result
View All Result
  • Home
  • NEWS
    • NEWS SHOW
    • NEWS
    • NEWS PROGRAM
  • PROGRAM AND FEATURE
    • Holiday
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • LIVE
  • English
    • English
    • Amharic

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

Welcome Back!

Login to your account below

Forgotten Password?

Create New Account!

Fill the forms bellow to register

All fields are required. Log In

Retrieve your password

Please enter your username or email address to reset your password.

Log In

Add New Playlist

Are you sure want to unlock this post?
Unlock left : 0
Are you sure want to cancel subscription?