አዲስ አበባ፣ ነሀሴ 12/2015፣ NBC ETHIOPIA -በዕለቱ ከሚደረጉ ውድድሮችም የሴቶች 10ሺ ሜትር ፍጻሜ በጉጉት ይጠበቃል እጅግ አጓጊውና በአትሌቲክስ ቤተሰቡ ዘንድ ተጠባቂ የሆነው ውድድር ምሽት 3 ሰዓት ከ55 ደቂቃ ጀምሮ ይከናወናል።

እአአ በ2021 በአስደናቂ ብቃት የዓለም ክብረወሰንን 29:01.03 በሆነ ሰዓት የሰባበረችው ጀግናዋ አትሌት ለተሰንበት ግደይ፤ አምና ኦሪጎን ላይ በተካሄደው ቻምፒዮና ያሳየችውን አስደናቂ አቋም ዘንድሮ ትደግማለች ተብሎ ይጠበቃል።
ዘንድሮ በ10ሺ ሜትር መወዳደር የጀመረችው ሌላኛዋ ኢትዮጵያዊት ኮከብ አትሌት ጉዳፍ ጸጋይ ለአሸናፊነት ከሚጠበቁ አትሌቶች አንዷ ነች። በዓመቱ በተካፈለችባቸው ውድድሮች ሁሉ ፈጣን ሰዓት በማስመዝገብ ያጠናቀቀችው ጉዳፍ በስፔን በተካሄደው የሰዓት ማሟያ ውድድር 29:29.73 የሆነ አራተኛውን ፈጣን ሰዓት አስመዝግባለች።
እንደ ኢፕድ ዘገባ በኢትዮጵያ በኩል ከ30 ደቂቃ በታች በሆነ ሰዓት የሚኒማ ማሟያውን የሮጡትና ከፈጣኗ አትሌት ጉዳፍ በጥቂት ሰከንዶች ብቻ ተከትለው የገቡት አትሌት እጅጋየሁ ታዬ እና ለምለም ኃይሉ በቻምፒዮናው ይሰለፋሉ። ወጣቶቹ አትሌቶች በቡድን ስራ እንዲሁም ለአሸናፊነት በሚደረገው ጥረት ሚናቸው ቀላል እንደማይሆን ይጠበቃል።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc












