አዲስ አበባ፣ ነሀሴ 12/2015፣ NBC ETHIOPIA -የዲጅታል የነዳጅ ግብይት ከተጀመረ አንስቶ 81 ቢሊዮን ብር የሚገመት ግብይት መፈጸሙን የነዳጅ እና ኢነርጂ ባለስልጣን አስታወቀ፡፡

የዘመናዊ ግብይት ተጠቃሚዎች በበኩላቸው ቴክኖሎጂው ከጥሬ ብር ክፍያ ጋር በተያያዘ ይገጥማቸው የነበረውን የጊዜ ብክነትና የደህንነት ስጋት እንዳስቀረላቸው ተናግረዋል።
ነዳጅን በዲጂታል ግብይት መፈጸም መንግሥት በከፍተኛ ድጎማ የሚያስገባውን ነዳጅ ከብክነት ለመከላከል፣ ቀልጣፋና ጊዜ ቆጣቢ አገልግሎት ለመስጠት እና ለቁጥጥር አመቺ እንዲሆን በማሳብ መሆኑ ይታወቃል።
በዲጅታል የነዳጅ ግብይት መፈጸም ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ በአገር አቀፍ ደረጃ 81 ቢሊዮን ብር የሚገመት ግብይት መፈጸሙን አቶ ለሜሳ ገልጸዋል፡፡
የዲጂታል ክፍያ ሥርዓቱ ከተጀመረ ወዲህ አብዛኛው ተጠቃሚ ወደ ሲስተሙ መግባቱን ማረጋገጥ መቻሉንና ከነዚህ ውስጥ ከ 99 በመቶ በላይ የሚሆኑ ተገልጋዮችም የዲጂታል ክፍያን በመጠቀም ግብይቱን እየፈጸሙ እንደሚገኙ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook –https://www.facebook.com/ethiopiannbc












