አዲስ አበባ፣ ነሀሴ 12/2015፣ NBC ETHIOPIA -የጤና ሚኒስቴር ከቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ህክምና እና ኮሌጅ ጋር በመተባበር ከፍለው መታከም ለማይችሉ የህብረተሰብ ክፍሎች ነፃ የጤና ምርመራ አገልግሎት መርሐ ግብር አስጀምሯል።

የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ደረጄ ዱጉማ ዜጎች ተላላፊ ያልሆኑ እንደ ደም ግፊት፣ ጉበት፣ ስኳር እና ሌሎች የበሽታ አይነቶችን በነፃ መመርመር እና ህክምና ማግኘት እንደሚችሉ በመርሀግብሩ ላይ ተናግረዋል።
የጤና ሚኒስቴር በዘንድሮ አመት የክረምት በጎ ፍቃድ የጤና አገልግሎትን ከሀምሌ ወር ጀምሮ ማካሄድ የጀመረ ሲሆን ከ1ሚሊዮን በላይ ዜጎችን የጤና ምርመራ እና ህክምና እንዲያገኙ ለማድረግ እየሰራ መሆኑ በመርሃ ግብሩ ላይ ተነስቷል።
“በጎነት ለጤናችን” በሚል መሪ ቃል የክረምት በጎ ፍቃድ የጤና አገልግሎቱ ከሀምሌ 24 ጀምሮ መካሄድ የጀመረ ሲሆን በዛሬ እለት በተጀመረው ነፃ የጤና አገልግሎት ላይ ከ40ሺ በላይ ዜጎች የቅድመ ምርመራ እና ህክምና እንዲያገኙ ለማድረግ ታቅዷል።
በሀሴት ሀይሉ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook-https://www.facebook.com/ethiopiannbc












