
አዲስ አበባ፣ ነሀሴ 12/2015፣ NBC ETHIOPIA – የቡሄ በዓልን ምክንያት በማድረግ በየአካባቢው በሚከናወነው የችቦ ማብራት ስነ ስርዓት ወቅት ርችት መተኮስ የተከለከለ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡
የከተማችንን ሰላም በዘላቂነት ለማረጋገጥ የአዲስ አበባ ፖሊስ ከሌሎች የፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት ውጤታማ ተግባራትን እያከናወነ እንደሚገኝ ይታወቃል፡፡
ይህንኑ የፀጥታ ስራ በአግባቡ ለመምራትና ለመቆጣጠር ሲባል እንዲሁም አጋጣሚውን በመጠቀም ሊፈፀሙ የሚችሉ ህገ-ወጥ ድርጊቶችን ለመከላከል በቡሄ በዓል የችቦ ማብራት ስነ ስርዓት ወቅት ርችት መተኮስ ክልክል መሆኑን ህብረተሰቡ ተገንዝቦ አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርግ የአዲስ አበባ ፖሊስ መልዕክት ማስተላለፉን ኢ ፕ ድ ዘግቧል ፡፡
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc