አዲስ አበባ፣ ነሀሴ 12/2015፣ NBC ETHIOPIA -የኢትዮጵያ አየር መንገድ በቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርክ የአውሮፕላን የውስጥ አካላትን ለማምረት የሚያስችለውን ስምምነት ተፈራርሟል።

በስምምነት ፊርማው ላይ የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር አቶ ተመስገን ጥላሁን ባደረጉት ንግግር፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የአውሮፕላን አካላት የማምረት ስራን በማስፋፋት ያለውን የበረራ ልምድ በመጠቀም የበለጠ ውጤታማ እንዲሆን የሚያስችል ነው፤ የመጀመሪያው ምእራፍ ፕሮጀክት በ810 ሚሊየን ብር ይገነባል ብለዋ::
የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በመላ ሀገሪቱ ገንብቶ በሚያስተዳድራቸው 13 ኢንዱስትሪ ፓርኮች እና 1 ነጻ የንግድ ቀጠና ውስጥ አቅም ያላቸው የሀገር ውስጥ እና የውጭ ባለሃብቶችን በማስገባት በስራ እድል ፈጠራ፣ በቴክኖሎጂ ሽግግር፣ በውጭ ኢንቨስትመንት ፍሰት፣ ተኪ ምርት በማምረት እንዲሁም ለኢንዱስትሪያላይዜሽን ግብ መሳካት የበኩሉን ድርሻ በመወጣት ላይ እንደሚገኝ ተገልጿል ሲል ኢፕድ ዘግቧል።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc












