
አዲስ አበባ፣ ነሀሴ 10/2015፣ NBC ETHIOPIA – በዩክሬን ጦርነት መባባስ ምክንያት ትልቅ ስጋት ውስጥ ያለችው ፖላንድ ትልቅ ወታደራዊ ሰልፍ ማድረጓ ታውቋል ።
ከዚህ ጋር በተያያዘም የፖላንድ ጦር የሶቪየት ህብረትን ወራሪ ሀይል በዋርሶ ጦርነት ድል ያደረገበትን 103ኛ ዓመት አክብሯል። እንደ አልጀዚራ ዘገባ በ1920 በዋርሶ ጦርነት ላይ ፖላንድ በሶቭየት ቀይ ጦር ላይ ላይ ድል የተቀዳጀችበት ዕለት ነበር ፡፡
በሌላ በኩል የሩስያ ከፍተኛ ባለስልጣናት ፖላንድ የዩክሬንን አንዳንድ ክፍሎች ለመያዝ ፍላጎት እያሰየች መሆኑን እየገለጹ ቢሆኑም ፤ የሩሲ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ማሪያ ዛካሮቫ ምንም ዓይነት ማስረጃ ሳይኖር በሞስኮ የሚነሳውን ፅንሰ-ሀሳብ ብዙ ጊዜ በማስተጋባት ፐሮፖጋንዳ እየተናገሩ ነው በማለት እየተተቹ ነው ።
በቶማይ መኮንን
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc