አዲስ አበባ፣ ነሀሴ 10/2015፣ NBC ETHIOPIA – ኢትዮጵያ ከፊሊፒንስ ጋር ያላትን የሁለትዮሽ ግንኙነት ለማጠናከር እንደምትሻ በፊሊፒንስ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሆነው የተሰየሙት ደሴ ዳልኬ ገለጹ።

አምባሳደር ደሴ የሹመት ደብዳቤያቸውን ለፊሊፒንስ ፕሬዝዳንት ፈርዲናንድ ሮሙዋልዴዝ ማርኮስ ጁኒየር አስገብተዋል።
ኢትዮጵያ እና ፊሊፒንስ ንግድና ኢንቨስትመንትን ጨምሮ በተለያዩ መስኮች ያላቸውን ትብብር ማስፋት የሚችሉባቸው አማራጮች እንዳሉ አምባሳደሩ ገልጸዋል።
ኢትዮጵያ ፊሊፒንስ ጋር ካላት የልማት እድገት፣የንግድ እና ኢንዱስትሪ መስኮች ልምድ መቅሰም እንደምትፈልግምና ያላትን የሁለትዮሽ ግንኙነትም ለማጠናከር እንደምትሰራ ተናግረዋል።
የፊሊፒንስ ፕሬዝዳንት ፈርዲናንድ ሮሙዋልዴዝ ማርኮስ ጁኒየር ሁለቱ አገራት ያላቸውን ትብብር ለማጠናከር መስራት እንደሚገባቸው መግለፃቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook-https://www.facebook.com/ethiopiannbc