
አዲስ አበባ፣ ነሀሴ 09/2015፣ NBC ETHIOPIA – በህጋዊ ንግድ ሽፋን የውጪ ሀገራት ገንዘቦችን የመመንዘር ህገ ወጥ ድርጊት ሲፈፅሙ የነበሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸው ይገኛል።
ተጠርጣሪዎቹ ህገ ወጥ ድርጊቱን ሲፈፅሙ የቆዩት በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 ኤልፓ ተብሎ በሚጠራው አካባቢና በወረዳ 5 ቄራ አካባቢ እንደሆነ ታውቋል።
በልብስ መሸጫና በመኪና እቃ መለዋወጫ ሱቆች ውስጥ የሚከናወን ህጋዊ ንግድን እንደ ሽፋን በመጠቀም የውጪ ሀገራት ገንዘቦችን በሱቆቹ ውስጥ ሲመነዝሩ ነበር ተብለው በቁጥጥር ስር የዋሉት አምስት ግለሰቦች ናቸው።
ህብረተሰቡ በሰጠው ጥቆማና ፖሊስ ባደረገው ክትትል ተጠርጣሪዎቹ ከተያዙ በኋላ በሁለቱ ሱቆች ውስጥ ብርበራ ከተካሄደ በኋላ 4 ሺህ 250 የአሜሪካ ዶላር ፣ 230 ዩሮ፣ 350 የሳውዲ ሪያል እና ከ226 ሺ የተገኘ መሆኑን ኢ.ፕ.ድ በዘገባው ገልጿል፡፡
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
See insights and ads
Like
Comment
Share












