አዲስ አበባ፣ ነሀሴ 09/2015፣ NBC ETHIOPIA – የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን(ኢጋድ) የሴቶች የሰላምና ደህንነት ፎረምን በይፋ ወደ ስራ የሚያስገባ ውይይት ዛሬ በኬንያ ናይሮቢ መካሄድ ጀምሯል።

በውይይቱ ላይ የኢጋድ ባለስልጣናት፣ የተቋሙ አባል አገራት ተወካዮች፣ የሲቪክ ተቋማትና ባለድርሻ አካላት ተሳታፊ ሆነዋል።
የውይይቱ ዓላማ የኢጋድ የሴቶች የሰላምና ደህንነት ፎረምን በይፋ ወደ ስራ እንዲገባ ማድረግ መሆኑ ተገልጿል።
የፎረሙ ስራ መጀመር ኢጋድ ለስርዓተ ጾታ እኩልነት እና ሴቶችን ማብቃት ላይ ያለውን ቁርጠኝነት የሚያሳይ መሆኑም ተመላክቷል።
የፎረሙ መመስረትም ለአንድነት፣ ለውይይት እና ለለውጥ ምቹ ሁኔታ ይፈጥራል ተብሎ እንደታመነበትም ተገልጿል። ውይይቱ እስከ ነገ እንደሚቆይ ከኢዜአ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc












