
አዲስ አበባ፣ ነሀሴ 09/2015፣ NBC ETHIOPIA – በደቡባዊቷ ሩሲያ ዳግስታን አካባቢ በሚገኝ የነዳጅ ማደያ ላይ በደረሰ ፍንዳታ 30 ሰዎች መሞታቸው ሲታወቅ 100 የሚሆኑ መቁሰላቸው ተገልጿል ።
ፍንዳታው የተከሰተው በካስፒያን ባህር ዳርቻ በምትገኘው በክልሉ መዲና ማካችካላ ከተማ ውስጥ ነው ።
በፍንዳታው ምክንያት የተጎዱ ሰዎችን ለማዳን ሄሊኮፕተርን ጨምሮ 260 ያህል የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች መሰማራታቸውን የሀገሪቱ የድንገተኛ አደጋ ሚኒስቴር አስታውቋል። በአደጋው ከሞቱት መካከል ሶስት ህጻናት እንደሚገኙበት አናዶሉ ዘግቧል ፡፡
በቶማይ መኮንን
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Like
Comment
Share