አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 3 /2015 | NBC ETHIOPIA-በባንግላዲሽ ኮክስ ባዛር እና ደቡብ ምስራቅ ባንዳርባን በጣለው ከባድ ዝናብ እና የመሬት መንሸራተት አራት ስደተኞችን ጨምሮ ቢያንስ ሰባት ሰዎች መሞታቸው ታውቋል።

በኮክስ ባዛር የሚገኘው የእሳት አደጋ አገልግሎት እና የሲቪል መከላከያ ዲፓርትመንት ምክትል ረዳት ዳይሬክተር አቲሽ ቻክማ በመሬት መንሸራተት ምክንያት አንድ ሰው መቁሰሉን እና ሌላ አንዲት እናት ከ ልጇ ጋር በሮሀኒንጋ የስደተኞች ካምፕ ህይወታቸው ማለፉ አረጋግጠዋል ፡፡

ሙዚቡር ራህማን የተባሉ የፖሊስ መኮንን በበኩላቸው በኮክስ ባዛር ርቆ በሚገኘው የቻካሪያ መንደር ውስጥ የተራራው ክፍል ከተደረመሰ በኋላ ሁለት ተጨማሪ ልጆች ህይወታቸው ሲያልፍ ሌላ ግለሰብ በተመሳሳይ ወንዝ ሲሻገር ህይወቱ እንዳለፈ ተናግረዋል።
በባንዳርባን ወረዳ በአሊካዳም በደረሰ የመሬት መንሸራተት ደግሞ ሁለት ተጨማሪ የሮኒንጋ ነዋሪዎች ህይወት ማለፉን የስደተኞች የእርዳታ አስተባባሪ ኮሚሽነር መሀመድ ሚዛኑር ራህማን መናገራቸውን አናዶሉ ዘግቧል።
በሃና ተሰማ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook-https://www.facebook.com/ethiopiannbc











