
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 2 /2015 | NBC ETHIOPIA የአሜሪካ መንግስት በኒጀር የተካሄደውን መፈንቅለ መንግሥት በዲፕሎማሲ እንዲያልቅና የቀድሞው ፕሬዝዳንት ሞሃመድ ባዙም ወደ ሥልጣናቸው እንዲመለሱ ቅድመ ሀሳብ ያቀረበች ሲሆን ልጊዜው ለሀገሪቱ የምትሰጠውን እርዳታ ማቋረጧን አስታውቃለች ።
ውይይቱ በጣም ግልጽ ነገር ግን ውስብስብ እንደነበር የአሜሪካ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ቪክቶሪያ ኑላንድ ተናግረዋል፡፡

የምዕራብ አፍሪካ የንግድ ማህበረሰብ ኢኮዋስ በበኩሉ እስከ ፊታችን እሁድ ወታደራዊው ጁንታ ሥልጣኑን ለቀድሞው ፕሬዝዳንት እንዲያስረክብ የጊዜ ገደብ ማስቀመጡ ተሰምቷል። ይህን ተከትሎ የመፈንቅለ መንግሥቱ መሪ ወታደራዊ ጁንታ ማስፈራሪያ መልክት በመላክ ምላሽ መስጠቱን አልጀዚራ ዘግቧል።
በቶማይ መኮንን
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc









