አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 2 /2015 | NBC ETHIOPIA- በጆርጅ ፍሎይድ ግድያ የተከሰሰው አራተኛው እና የመጨረሻው የሚኒያፖሊስ ፖሊስ ቱ ታኦ ከአራት ዓመት በላይ እስራት እንደተፈረደበት አናዶሉ ዘግቧል።

ታኦ እ.ኤ.አ. ግንቦት 25 ቀን 2020 በሚኒሶታ ግዛት ውስጥ ግድያው ከተፈፀመበት ቦታ የነበሩ ተመልካቾች ፎቶ እንዳያነሱ ሲከለክል እንደነበር ታውቋል ።
ዳኛው በግንቦት ወር ፍሎይድ ለሞት እንዲዳደረግ በማድረጉ የፖሊስ መኮንኑን ጥፋተኛ ነው ብለውታል ፡፡
ፍሎይድ ለመሞት እያቃሰተ “መተንፈስ አልችልም” እስኪል ድረስ የቀድሞ መኮንን ዴሪክ ቻውቪን የፍሎይድ አንገት ላይ ለ10 ደቂቃ ያህል ተንበርክኮ እንደነበር የሚታወስ ነው ።
በሃና ተሰማ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc










