የውሃ ፕሮጀክቶቹ የከተማዋን እለታዊ የውሀ ምርትና ስርጭት እንዲሁም የፍሳሽ ማስወገድ አቅም ከፍ የሚያደርጉ ሲሆን እስከ 5 መቶ ሜትር ጥልቀት ያላቸው በቀን 67ሺህ ሜትር ኪዩብ ውሃ መስጠት የሚችሉ 25 የውሀ ጉድጓዶች ናቸው፡፡
የውሀ ጉድጓዶቹ የኤሌክትሮ ሜካኒካል ስራዎች፣ 31 ኪሎ ሜትር የተለያዩ ስፋት ያላቸው የውሀ መስመር ዝርጋታ እና እስከ 1500 ሜትር ኪዩብ የመያዝ አቅም ያላቸው የማጠራቀሚያ ጋን ስራ የተከናወናላቸው ሲሆን የከተማዋን ዕለታዊ ውሀ የማምረት አቅም ወደ 792 ሺህ ኪዩቢክ ሜትር ከፍ የሚያደርጉ ይሆናል፡፡
ለጋራ መኖሪያ ቤቶች 138 ኪሎ ሜትር የፍሳሽ እና 40 ኪ/ሜ የተለያዩ መጠን ያላቸው የውሀ ማስተላለፊያ መስመሮች ዝርጋታም ተጠናቅቆ ለአገልግሎት ዝግጁ ሆኗል፡፡
ውሀ ከማምረትና ከማሰራጨት ባሻገር ለሕብረተሰቡ የሚሰራጨውን ውሀ ደህንነት የሚያረጋግጥ የውሃ እና ፍሳሽ ላብራቶሪ ተቋቁሞ ለአገልግሎት ዝግጁ ተደርጓል፡፡
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
#NBC_ETHIOPIA
#ሆኖ_መገኘት