
ሚኒስትር ዴኤታው ወቅታዊውን የአገሪቱን የዲፕሎማሲ ሁኔታ አስመልክተው ዛሬ በሰጡት ማብራሪያ፣ በሰላም በሁለትዮሽና በባለብዙ ወገን ግንኙነትት ላይ ተመስርቶ በስፋት እየተሰራ ያለውና ወደ አዲስ ምእራፍ የተሸጋገረው የውጭ ግንኙነት ስራ ውጤታማ ሆኗል ብለዋል።
የአለም ባንክ ፕሬዚዳንት በኢትዮጵያ ያደረጉት ጉብኝት ለአገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርም ትግበራ አዎንታዊ ሚና እንዳለውም አስታውቀዋል።
ኢትዮጵያ በጐረቤት አገራት፣ በአፍሪካና አለም አቀፍ ደረጃ በሰላምና ቀጣናዊ ትስስር ረገድ ሰፋፊ የዲሞክራሲ ስራዎችን እያከናወነች መሆኗን የገለጹት አምባሳደር ምስጋኑ፣ በተለይ ከፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት ወዲህ በአካባቢያዊ ጉዳዮች ያላት የመሪነት ሚና ወጤታማ መሆኑን ተናግረዋል።
የተለያዩ አገራት መሪዎች እያደረጉት ያለው ጉብኝት ኢትዮጵያ በዲፕሎማሲው መስክ ትኩረት የምትስብ መሆኗን ያሳያል ብለዋል።
አዲሱ የዲፕሎማሲ ስራ ትኩረቱን በልማትና ኢኮኖሚ ላይ ያደረገ መሆኑን ጠቅሰው፣ በተለይም የአለም ባንክ ፕሬዚዳንት አጃይ ባንጋ በኢትዮጵያ ያደረጉት ጉብኝት የአገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርም ለማስፍጸምና የፋይናንስ ትብብር ለማድረግ ትልቅ ሚና ያለው እንደሆነም አብራርተዋል። የዲፕሎማሲ ግንኙነት አድማሱን በማስፋት አዲሱ የዲፕሎማሲ ትብብር ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም መግለፃቸውን ኢፕድ ዘግቧል ።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook-https://www.com/ethiopiannbc
#NBC_ETHIOPIA
#ሆኖ_መገኘት











