
ባንኩ በኢትዮጵያ እየተተገበረ ያለውን የኢኮኖሚ ማሻሻያ ለማሳካት የሶስት ዓመት መርሐ-ግብር ዝግጅት በማጠናቀቅ ላይ መሆኑንም ገዢው ገልጸዋል።
የማክሮ ኢኮኖሚ መረጋጋትን ለማረጋገጥ የፊስካል ፖሊሲ አተገባበርን ውጤታማ ማድረግ፣ ጥብቅ የገንዘብ ቁጥጥርን ማጠናከር እንዲሁም የውጭ ምንዛሬ መረጋጋትን መፍጠር እንደ ግብ መያዛቸውን አመልክተዋል።
በዚህም የዋጋ መረጋጋትን ለማምጣት በትኩረት እንደሚሰራ ጠቅሰው የፋይናንስ ተቋማት አገልግሎታቸውን እንዲያሻሽሉ፣ የዲጂታል አሰራራቸውን እንዲያፋጥኑና የፋይናንስ አካታችነትን እንዲያስፋፉ ጥብቅ ቁጥጥር በማድረግ ላይ መሆኑን መናገራቸውን ኢፕድ ዘግቧል።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook.com/ethiopiannbcn.com/news/
#NBC_ETHIOPIA
#ሆኖ_መገኘት












