
ለአፍ ውሰጥ ካንሰር የተለያዩ አጋላጭ ምክንያቶች ሊጠቀሱ ቢችሉም በቀጥታ ግን የአፍ ውስጥ ካንሰር በዚህ ነው የሚመጣው ተብሎ የተለየ ተጨባጭ መንስኤ እስካሁን አልተገኝም።
ነገር ግን በጥናት እንደተረጋገጠው ለአፍ ውስጥ ካንሰር እንደ መንስኤ የተለያዩ አጋላጭ ምክንያቶች የተቀመጡ ሲሆን ከነዚህም ወስጥ ዋነኞቹ በቅደም ተከተል እንደሚከተለው ተዘርዝረዋል፡፡
????ሲጋራ/ትምባሆ

ጥናቶች እንደሚያሳዩት እስከ 90% የአፍ ውስጥ ካንሰር ተጠቂዎች የአሁን ወይም የቀደመ የትምባሆ መጠቀም ታሪክ ያላቸው ናቸው።
ትምባሆን በሲጋራ መልኩ በማጨስም ይሆን በጉንጭ ቅጠሉን በመያዝ እንዲሁም በሌላ መልኩ በአፍ ውስጥ መጠቀም አጋላጭ ምክንያት ነው።
ሲጋራ/ትምባሆ ተጠቃሚዎች ከ2-12 እጅ በላቀ ሲጋራ ከማይጠቀሙት በላይ በአፍ ውስጥ ካንሰር የመያዝ እድላቸው ከፍ ያለ ነው።
????አልኮል መጠጥ

አልኮል ተጠቃሚዎች ከማይጠቀሙት በበለጠ በአፍ ውስጥ ካንሰር የመያዝ እድላቸው የሰፋ ነው፡፡ አንዳንድ ጥናቶች እንደሚያሳዩት 75% የአፍ ውስጥ ካንሰር ተጠቂዎች በተለያየ ደረጃ የአልኮል ተጠቃሚነት ታሪክ ያላቸው ሆኖ ተገኝተዋል። ሲጋራ እና አልኮል መጠጥ በዋነኛነት የአፍ ውስጥ ካንሰር አጋላጭ ምክንያቶች ሲሆኑ ሁለቱንም በጋራ የሚጠቀሙ ሰዎችም በአፍ ውስጥ ካንሰር የመያዝ ዕድላቸው እጅግ የሰፋ ይሆናል አንዳንድ ጥናቶች እንደሚያሳዩት እስከ 22 እጅ እንደሚጨምር ይጠቁማሉ።
????የቫይረስ ኢንፌክሽኖች

በዋነኛነት HPV, EBV… ተጠቃሽ ሲሆኑ ይበልጥ ከጉሮሮ ካንሰሮች ጋር በተያያዘ አጋላጮች ናቸው።
????የህክምና እና የፀሀይ ጨሮች

የፀሀይ ጨረር ለቆዳ እና ከንፈር አካባቢ ካንሰሮች ሊያጋልጥ ሲችል የህክምና ጨረር ለምራቅ አመንጪ አካላት ካንሰር በዋነኛነት ያጋልጣል።
????የአፋችንን ውስጥ ስጋዎች በተደጋጋሚ እና ለረዥም ጊዜ ሊያስቆጡ የሚችሉ ነገሮች (መቆጣት= ማበጥ: መቅላት: መላጥ; ህመም..)

-መጥፎ የአፍ ውስጥ ንፅህና/የአፍ ውስጥ መቆሸሽ
-በትክክል ያልገጠሙ ሰው ሰራሽ ጥርሶች
-አንዳንድ የአፍ ውስጥ መጉመጥመጫዎች ከያዟቸው አንዳንድ ንጥረ ነገሮች ምክንያት
-ሌሎች በአፋችን ውስጥ በተደጋጋሚ የምንጠቀማቸው/ የምንይዛቸው ነገሮች ቅጠሎች፤ ዕፆች፤ ኬሚካሎች
????ያልተመጣጠነ ምግብ እና የሰውነት የበሽታ መከላከል አቅም መቀነስ

-የቫይታሚን A እና B እጥረት
-HIV
????እድሜ

-በአብዛኛው እድሜ በገፋ ቁጥር በአፍ ውስጥ ካንሰር የመያዝ እድሉም ይጨምራል
-ነገር ግን አንዳንድ ጥናቶች እንደሚጠቁሙት ከድህነት ወለል በታች በሚገኙ ሀገራት የአፍ ውስጥ ካንሰር ገና በለጋነት/ወጣትነት እድሜ ላይ በብዛት እየተሰተዋለ ነው
????በዘር
በቤተሰብ ውስጥ ከዚህ በፊት ተከስቶ ከነበረ በአፍ ውስጥ ካንሰር የመያዝ እድሉ ቤተሰብ ተከስቶበት ከማያውቀው /የጨመረ ነው
????ሌሎችም
ከላይ የተጠቀሱት አጋላጭ ምክንያቶች አሉ ማለት የግድ በአፍ ውስጥ ካንሰር እንያዛለን ማለት እንዳልሆነ እነዚህ አጋላጮች የሉብንም ማለትም በካንሰር ላለመያዝ ዋስትና አይሆንም፡፡
በዘርፉ በየግዜው ብዙ አዳዲስ ጥናቶች እና ግኝቶች እየወጡ እና ምክንያቶቹም ሙሉ በሙሉ ጨርሰው ገና ያልታወቁ መሆኑን ልብ ማለት ይገባል ።
በካንሰር ላለመያዝ ምንም አይነት ዋስትና የለንም! ሁሉም ሰው ሰው ሆኖ በዚች ምድር እስካለ ድረስ መጠኑ ይበዛም ይነስም በካንሰር የመያዝ እድል አለው። ነገር ግን በጥናት የታወቁ አጋላጭ መንሴዎችን በመራቅ እና በመከላከል በካንሰር የመያዝ እድላችንን በከፍተኛ መጠን መቀነስ እንችላለን!!
በሃና ተሰማ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
#NBC_ETHIOPIA
#ሆኖ_መገኘት












