
225 ኩንታል የአፈር ማዳበሪያና ከ16 ሰው በላይ ጭኖ ጉዞውን ከደባርቅ ጃናሞራ አድርጎ ሲጓዝ የነበረው የጭነት መኪና መካነ-ብርሃን ከተማ ከመድረሱ በፊት ደበላ አካባቢ መንገዱን ስቶ መገልበጡን የሰሜን ጎንደር ኮሙኒኬሽን ማስታወቁን ኢ.ፕ.ድ ዘግቧል።

የስምንቱ ሰዎች ህይዎት ወዲያውኑ ሲያልፍ ከአራት ሰዎች በላይ ከባድ የአካል ጉዳት ደርሶባቸው በጃናሞራ እና ደባርቅ ሆስፒታል ህክምና እየተከታተሉ ናቸው።
አደጋው የተከሰተው ከረፋዱ 4:00 ሰአት አካባቢ ሲሆን ሰወቹ አብዛኛው የተሳፈሩት ቧሂት መገንጠያ ሲሆን የሴፍትኔት የእርዳታ ብር ለማውጣት የመጡ አርሶ አደሮች እንደነበሩ ለማወቅ ተችሏል።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
#NBC_ETHIOPIA
#ሆኖ_መገኘት









