
አዲስ አበባ ፤ ሐምሌ 19/2015 NBC Ethiopia- በሸገር ከተማ ቡራዩ ክፍለ ከተማ ከታ ወረዳ 2 የእንጀራ ልጆቿን በአሰቃቂ ሁኔታ ገድላ ያቃጠለችው ግለሰብ የሞት ፍርድ ተፈረደባት።
የሸገር ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዛሬ ባዋለው ችሎት የ2 ዓመትና የ12 ዓመት የእንጀራ ልጆቿን ሆን ብላ እና ጨለማን ተገን አድርጋ በቀን 27/08/2015 ዓ.ም ከለሊቱ 5:00 ላይ በመጥረቢያ ቆራርጣ ገድላ ያቃጠለችው ወ/ሮ ነጋሴ ከበደ በሞት ፍርድ እንድትቀጣ ውሳኔ እንዳስተላለፈ ኢቢሲ ዘግቧል።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc