
አዲስ አበባ ፤ ሐምሌ 19/2015 NBC Ethiopia- ጣሊያን ማክሰኞ ዕለት በአስከፊ የአየር ጠባይ ሁኔታ ምክንያት በደቡብ ባለው ክልሎች ከፍተኛ ሙቀት እና ሰደድ እሳት እንዲሁም በሰሜን ሀይለኛ አውሎ ነፋስ እንዳጋጠማት የጣልያን ባለስልጣናት መናገራቸውን አናዱሉ ገልጿል። አስከፊው የአየር ሁኔታ አምስት ሰዎችን ሲገድል፤ በርካቶችን አቁስሏል ።
የሲሲሊ ዋና ከተማ የሆነችውን ፓሌርሞ አውሮፕላን ማረፊያዋን ለሰዓታት እንድትዘጋ የሰደድ እሳት አስገድዷታል፤ የእሳት አደጋ ተከላካዮች በአቅራቢያው በሚገኝ አካባቢ እሳቱን ለመቆጣጠር ሲሞክሩ የመንገድ እና የባቡር መንገዶች ተቋርጠዋል።
በቃጠሎው ምክንያት አምቡላንስ ወደ ቤታቸው መድረስ ባለመቻሉ አንዲት የ88 ዓመቷ ሴት ህይወታቸው ማለፉን ታውቋል።

በፓሌርሞ አየር ማረፊያ አቅራቢያ በሲኒሲ አካባቢ በሚገኝ ትንሽ ቤት ውስጥ ሁለት አስከሬኖች ተገኝተዋል፡፡የነፍስ አድን ሰራተኞች እንደተናገሩት ሁለቱ በ70ዎቹ የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ እና በእሳት ነበልባል የተገደሉ ናቸው ብለዋል ።
በሌላኛው የደቡብ ክልል ካላብሪያ የሚኖሩ የ98 ዓመት አዛውንት በሰደድ እሳት ቃጠሎው ህይወታቸው አልፏል።
በካታኒያ የሚገኘው አውሮፕላን ማረፊያ ባለፈው ሳምንት በአንድ ተርሚናል ህንፃ ላይ በተነሳ የእሳት ቃጠሎ ምክንያት የተዘጋ ሲሆን በቅርቡ ለጥቂት በረራዎች ክፍት ሆኗል። በተጨማሪም ፓሌርሞ እና ካታኒያ ሁለቱም የመብራት እና ውሀ አቅርቦት መቆራረጥ ገጥሟቸዋል፡፡
በሰሜን ጣሊያን የፋይናንስ ዋና ከተማ በሆነችው ሚላን ፤ አውሎ ንፋስ ቀላቅሎ በጣለው ዝናብ ጣራ ገነጣጥሎ በመቶዎች የሚቆጠሩ ዛፎችን ከስሩ በመንቀል መንገዶችን መዝጋቱ ታውቋል ። የትራንስፖርት ባለስልጣናት በከተማው የኤሌክትሪክ አውታር ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱን ተናግረዋል ። የ16 ዓመቷ ወጣት በሰሜን ብሬሻ ከተማ አቅራቢያ በስካውት ካምፕ ውስጥ አንድ ዛፍ በድንኳኗ ላይ በመውደቁ ምክንያት ሊያልፍ ችሏል።

ጣሊያን በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት ከፍተኛ የአየር ጠባይ ካጋጠማቸው የአውሮፓ ሀገራት አንዷ ስትሆን በግንቦት ወር በሰሜናዊ የሀገሪቱ ክፍል ሮማኛ ግዛት ገዳይ ጎርፍ ደርሶባታል።
በፕሪሚየር ጆርጂያ ሜሎኒ የሚመራው የቀኝ አክራሪ መንግስት በአስቸጋሪ የአየር ሁኔታ የተጠቁ ክልሎችን ለመርዳት የአደጋ ጊዜ እርምጃዎችን እያዘጋጀ መሆኑን ገልጿል ፣ሚላንን ጨምሮ ሰሜናዊው የሎምባርዲ ክልል ከ100 ሚሊዮን ዩሮ (110 ሚሊዮን ዶላር) በላይ ጉዳት እንደሚደርስ ተገምቷል ።
የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር ማቲዮ ፒያንቴዶሲ ባለስልጣናት በሰሜናዊ እና በደቡብ ክልሎች ያለውን ሁኔታ በቅርበት እየተከታተሉ መሆኑን ገልፀው ተጨማሪ የነፍስ አድን ሀይሎች መሰማራታቸውን አስታውቀዋል።
የሲቪል ጥበቃ ሚኒስትር ኔሎ ሙሱሜሲ በፌስቡክ ላይ “ይህ በጣሊያን ታሪክ ውስጥ ለ 10 ዓመታት በጣም አስቸጋሪ ከሆኑት ቀናት አንዱ ነው፤ የአየር ንብረት ለውጥ በሀገራችን ላይ ወድቋል እናም ሁላችንም መንገዳችንን እንድንቀይር ይጠበቃል፤ ምንም ሰበብ የለም ብለዋል፡፡
በመጨረሻም በርካታ ክልሎች መንግስት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲያውጅ ጥያቄ ማቅረባቸው ታውቋል ።
በሃናተሰማ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
#NBC_ETHIOPIA
#ሆኖ_መገኘት